ቶጎ የቅኝ ግዛት ዘመን የቀን መቁጠሪያን በማስወገድ የአፍሪካ አዲስ ዓመት እንዲታወጅ ጥሪ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopiaቶጎ የቅኝ ግዛት ዘመን የቀን መቁጠሪያን በማስወገድ የአፍሪካ አዲስ ዓመት እንዲታወጅ ጥሪ አቀረበች
ቶጎ የቅኝ ግዛት ዘመን የቀን መቁጠሪያን በማስወገድ የአፍሪካ አዲስ ዓመት እንዲታወጅ ጥሪ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.02.2026
ሰብስክራይብ

ቶጎ የቅኝ ግዛት ዘመን የቀን መቁጠሪያን በማስወገድ የአፍሪካ አዲስ ዓመት እንዲታወጅ ጥሪ አቀረበች

ሀገሪቱ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመተባበር የአፍሪካ አዲስ ዓመትን ጨምሮ ሌሎች አኅጉራዊ በዓላት የሚታወጁበትን ሁኔታ በተመለከተ ከባለሙያዎች ጋር ውይይት ለመጀመር ማቀዷን የቶጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የቅኝ ግዛት ፖሊሲዎች የአፍሪካን ማንነት አዛብተውታል ሲል ሚኒስቴሩ በመግለጫው አጽንኦት ሰጥቷል።

በመሆኑም በአዲሱ የባለብዙ ዋልታ ዓለም ውስጥ የአፍሪካ ስልታዊ ግቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

የቀን አቆጣጠር ሉዓላዊነትን ማስመለስ፣

የጥንታዊ የጊዜ አቆጣጠር ሥርዓቶችን ወደ ነበሩበት መመለስ፣

የአፍሪካ በዓላት እንደ ቻይናውያን አዲስ ዓመት ወይም እንደ አይሁዳውያን "ሮሽ ሃሻና" ሁሉ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና እንዲያገኙ ማድረግ።

በቶጎ፣ ሎሜ ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ማዘጋጀት እና የውሳኔ ሃሳቦችን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ማቅረብ ቀጣይ እርምጃዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0