የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የኢትዮጵያን የስንዴ ምርት ስኬት "ታሪካዊ ምዕራፍ" ሲል አወደሰ
13:31 25.02.2026 (የተሻሻለ: 13:34 25.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የኢትዮጵያን የስንዴ ምርት ስኬት "ታሪካዊ ምዕራፍ" ሲል አወደሰ
ኢትዮጵያ ከነበረችበት ጥገኝነት ወጥታ ስንዴን ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ ለመላው አፍሪካ ትልቅ ማሳያ ነው ማለቱን ጠቅሶ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
"አፍሪካ በየዓመቱ ለምግብ ምርቶች ግዢ ከ70 ቢሊዮን እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች፤ ከዚህ ውስጥ ስንዴ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ የኢትዮጵያ ተሞክሮ ይህንን ወጪ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት እንደሚቻል በተግባር አሳይቷል” ሲሉ የኅብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ሰማያዊ ኢኮኖሚ እና የዘላቂ አካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ሙሴ ቪላካቲ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽነሩ፤ ኅብረቱ የኢትዮጵያን ፈጣን ሽግግር በቅርብ ሲከታተል እንደቆየ በማንሳት፤ የተመዘገበውን ውጤት እጅግ አርኪና አስደናቂ የስኬት ታሪክ ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ተሞክሮ በመከተል የምግብ ደህንነታቸውን እንዲያጠናክሩ ኮሚሽነር ቪላካቲ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X