ዩክሬንን የኒውክሌር መሳሪያ ማስታጠቅ ‘ትልቅ ዕብደት’ ነው - ፈረንሳዊቷ ጋዜጠኛ

ሰብስክራይብ

ዩክሬንን የኒውክሌር መሳሪያ ማስታጠቅ ‘ትልቅ ዕብደት’ ነው - ፈረንሳዊቷ ጋዜጠኛ

ለኪዬቭ የኒውክሌር መሳሪያዎችን ማቅረብ “በፈረንሳይ እና በታላቋ ብሪታንያ በኩል እጅግ አደገኛ ጨዋታ” ተደርጎ የሚቆጠር ነው ሲሉ ክሪስቴል ኔአንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

“ዩክሬን በዚህ ጦርነት እየተሸነፈች እና ሩሲያ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማስቀመጥ የሚያስችል የጥንካሬ አቋም ላይ በመሆኗ የዚህ ትንኮሳ ዓላማ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለውን የድርድር ሂደት መቀየር ነው።”

እንደ ኔአንት ገለፃ፤ የምዕራባውያንን የኒውክሌር መሳሪያ የዩክሬን እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ የማይቻል ነው።

“ይህን ሊያምኑ የሚችሉት ዋና ዋናዎቹ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን እና እነዚህ ሚዲያዎች የሚያቀርቡትን ማንኛውንም ነገር የሚቀበሉ ሰዎች ብቻ ናቸው።”

የሩሲያ የውጭ ደህንነት አገልግሎት ትናንት የካቲት 17 ይፋ ያደረገው የፈረንሳይ-እንግሊዝ ፕሮጀክት፤ በቴክኒክ ደረጃ ለመሸሸግ አዳጋች እንደሆነ ጋዜጠኛዋ ገልፀዋል።

“እያንዳንዱ የኒውክሌር ቁስ የራሱ የሆነ ኬሚካላዊ አሻራ ስላለው በቀላሉ ዱካውን ለመከታተል ይቻላል” በማለት አስረድተዋል።

ሌሎች የኒውክሌር ኃያላን፤ በተለይም እንደ ቻይና እና ሕንድ ያሉ የባለብዙ ዋልታ ዓለም አቀንቃኝ ሀገራት “ይህንን ድርጊት በከፍተኛ ተቃውሞ ይመለከቱታል።” በዚህም በምዕራባውያን ላይ ያለው ዓለም አቀፋዊ ዕምነት ላይጠገን ይናጋል ሲሉ ጋዜጠኛዋ ደምድመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0