ኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፉን ለውጭ አየር መንገዶች ክፍት እንደማታደርግ አስታወቀች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፉን ለውጭ አየር መንገዶች ክፍት እንደማታደርግ አስታወቀች

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን፣ የአገር ውስጥ የአቪዬሽን ዘርፍ በራሱ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የሚያስችል ተቋማዊና ተግባራዊ አቅም እስካልገነባ ድረስ ዘርፉን ለውጭ የግል አየር መንገዶች ሙሉ በሙሉ ክፍት የማድረግ ዕቅድ እንደሌለ አስታውቋል።

"የሀገር ውስጥ የግል አቪዬሽን ኩባንያዎች አሁንም በቁጥጥር ሥርዓቱና በሥራ እንቅስቃሴያቸው ላይ መዋቅራዊ ችግሮች አሉባቸው። ማስተካከያዎች እየተደረጉ ቢሆንም ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ ለመታየት ጊዜ ይወስዳል" ሲሉ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል።

አብዛኞቹ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በቅርቡ አውሮፕላኖችን ለባንክ ብድር በመያዣነት መጠቀም የሚያስችል የፖሊሲ ለውጥ መደረጉን እንደ አብነት ጠቅሰዋል።

ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ሊደረግ የሚችለው የአገር ውስጥ ኦፕሬተሮች በሚኖራቸው ጥንካሬና አስተማማኝ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋቱ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 12 ፈቃድ ያላቸው የግል አየር መንገዶች የሚገኙ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ኩባንያዎች ወደ ዘርፉ ለመግባት በሂደት ላይ መሆናቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ምስል ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0