በ2035 በአፍሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያስችል ባለ 10 ቢሊዮን ዶላር የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢኒሼቲቭ ተጀመረ

በ2035 በአፍሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያስችል ባለ 10 ቢሊዮን ዶላር የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢኒሼቲቭ ተጀመረ
ኢኒሼቲቩ ከመሠረታዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ጀምሮ በሥራ ፈጠራ፣ በክልላዊ የመረጃ ሥርዓቶች፣ በፖሊሲ ማዕቀፎች እና በክህሎት ልማት ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያለመ መሆኑን የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታውቋል።
በቅርቡ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የ2026 የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፎረም ማጠናቀቂያ ላይ ባንኩ ባወጣው መግለጫ፣ ግቡ አፍሪካን የሰው ሠራሽ አስተውሎት የፈጠራ ማዕከል ማድረግ ሲሆን፣ ይህም በአገር በቀል እሴት ግንባታ እና አካታች እድገት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ ነው ብሏል።
ዋና ዋና የትኩረት መስኮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
🟠 የሥራ ዕድል ፈጠራ፦ በሰው ሠራሽ አስተውሎት በሚመራ የሥራ ፈጠራ እና የሰው ኃይል ክህሎትን በማሳደግ እስከ 2035 ድረስ 40 ሚሊዮን አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር።
🟠 ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ፦ በአፍሪካ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ላይ የ1 ትሪሊዮን ዶላር ጭማሪ ያስገኝል ተብሎ ይገመታል።
🟠 የኢንቨስትመንት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች፦ ፋይናንሱ የመረጃ ሥነ-ምህዳሮችን፣ የኮምፒዩቲንግ መሠረተ ልማቶችን፣ የክህሎት ልማትን፣ የሥነ-ምግባር አሠራርን እና የሙከራ ፕሮጀክቶችን ይደግፋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X