ግብፅ ለኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር የማግኘት ዕቅድ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

© telegram sputnik_ethiopiaግብፅ ለኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር የማግኘት ዕቅድ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች
ግብፅ ለኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር የማግኘት ዕቅድ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.02.2026
ሰብስክራይብ

ግብፅ ለኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር የማግኘት ዕቅድ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

ግብፅ በናይል ውኃ አጠቃቀም ላይ ከስምምነት ከተደረሰ፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ ከአፍሪካ አጋሮቿ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ዘ ናሽናል የተባለው የመካከለኛው ምስራቅ ሚዲያ የካይሮ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ግብፅ ይህን በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተን የአጋርነት ጥያቄ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለዋሽንግተን ባሳለፍነው ሳምንት ማቅረቧ ተጠቁሟል።

ይህ ጥያቄ ግብፅ በሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ እና ኤርትራ ያላትን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ በመጠቀም፣ ስምምነት ካልተደረሰ የኢትዮጵያን የባሕር በር አማራጮች ልትዘጋ እንደምትችል የሚጠቁም "ውስጠ-ወይራ ማስጠንቀቂያ" እንደያዘ ተነግሯል።

የግብጽ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ መግለጫዎች፣ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን በመጥቀስ "ታሪካዊ መብቶች" ላይ መተማመናችውን የሚያሳይ ነው ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ ኮንኗል፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ባስተላለፉት መልዕክት፤ የውኃ ሀብትን ለልማት ማዋል የሌሎችን ድርሻ መቀነስ ማለት እንዳልሆነና ወንዙ ለግጭት ሳይሆን ለትብብር ሊያገለግል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የባሕር በር ለኢትዮጵያ ያለውን አስፈላጊነትም በዚሁ መልዕክታቸው አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡

ግብፅ በጅቡቲና ኤርትራ የሚገኙ ወደቦችን ለማልማት ስምምነት ላይ የደረሰች ሲሆን፣ ይህ እርምጃ በግድቡ ድርድር ላይ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የታለመ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ፣ ግብጽ አቅርባዋለች ስለተባለው የድጋፍ ሐሳብ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0