ኢትዮጵያዊቷ ሠዓሊ ሰላማዊት ገብረፃድቅ የሥዕል ሥራዎቿን በሞስኮ ለዕይታ አቀረበች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያዊቷ ሠዓሊ ሰላማዊት ገብረፃድቅ የሥዕል ሥራዎቿን በሞስኮ ለዕይታ አቀረበች

ኢትዮጵያዊቷ አርቲስት ሰላማዊት ገብረፃድቅ ከዓለም ሕዝቦች ጉባኤ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው የሥነ-ጥበብ ዐውደ-ርዕይ በሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ በደማቅ ሁኔታ ተከፍቶ ለዕይታ ቀርቧል።

ባሳለፍነው አርብ (የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም) የዐውደ-ርዕዩ መክፈቻ እና የአርቲስቷ የጥበብ አልበም ምርቃት፤ በሩሲያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዶ/ር ገነት ተሾመ በተገኙበት በሞስኮ ተከናውኗል።

ሰዓሊ ሰላማዊት በዐውደ-ርዕዩ ላይ ለተገኙ ጎብኚዎች ስለ ሥራዎቿ ጥልቅ ማብራሪያ የሰጠች ሲሆን፣ ስራዎቿም በጎብኚዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፈዋል።

የሰላማዊት የጥበብ አልበም በይፋ የማስመረቅ ሥነ-ስርዓት ነገ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በዓለም ሕዝቦች ጉባኤ አዳራሽ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0