የሩሲያ የላይኛው ምክር ቤት እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ለዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ለማቅረብ የያዙትን ዕቅድ እንዲመረምሩ አሳሰበ

የሩሲያ የላይኛው ምክር ቤት እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ለዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ለማቅረብ የያዙትን ዕቅድ እንዲመረምሩ አሳሰበ
የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ ፓርላማዎች በአስቸኳይ ተገቢውን የፓርላማ ምርመራ መጀመር አለባቸው፤ በውጤቱም ላይ በመመሥረት ስለዚህ "እጅግ አደገኛ እና ግድ የለሽ" ድርጊት ሁኔታዎች ለዜጎቻቸውና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳወቅ አለባቸው፤ ሲል የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ባወጣው ጥሪ ገልጿል።
ዛሬ ቀደም ብሎ፣ የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት እንግሊዝ እና ፈረንሳይ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ለኪዬቭ ለማስተላለፍ እየተዘጋጁ መሆኑን ይፋ አድርጎ ነበር።
በጥሪው ላይ የቀረቡ ቁልፍ ማስጠንቀቂያዎች፦
ለዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ማቅረባቸው ግጭቱን ያባብሰዋል፤ ቀጣናዊ ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላል፡፡
መሰል የዲሞክራሲያዊ ተቋማትን የመዝለል ተግባር "በአደጋ የተሞላ ነው፡፡"
በሩሲያ የኒውክሌር ዶክትሪን መሠረት፣ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ በሌለው ሀገር የሚፈጸም ጥቃት በኒውክሌር ኃያል ሀገር ድጋፍ ከታጀበ እንደ የጋራ ጥቃት ስለሚቆጠር፣ የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ ሕዝቦች ሳይወዱ በግድ ለአደጋ ይጋለጣሉ፡፡
ይህ ጥሪ ለእንግሊዝ፣ ለፈረንሳይ እና ለአውሮፓ ሕብረት ፓርላማዎች እንዲሁም ለተባበሩት መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እና ለኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች አለመስፋፋት ስምምነት ክለሳ ጉባኤ የተላከ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት እና የአቶሚክ ኤጀንሲ ስለ ዕቅዱ ምርመራ እንዲያደርጉም ሐሳብ አቅርቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X