ኢትዮጵያ በ2030 የኤሌክትሪክ መኪኖች ፋብሪካዎቿን 60 ለማድረስ አቅዳለች – የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
12:07 24.02.2026 (የተሻሻለ: 12:34 24.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ2030 የኤሌክትሪክ መኪኖች ፋብሪካዎቿን 60 ለማድረስ አቅዳለች – የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
አሁን በአገሪቱ 17 የኤሌክትሪክ መኪኖች ገጣጣሚ ፋብሪካዎች እየሠሩ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን መንግሥት እስከ 2032 500 ሺህ ኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለማስገባት ውጥን መያዙን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
"ኢንቨሰትመንትን ለመሳብ መንግሥት ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መኪኖችን በሀገር ውስጥ ለሚገጣጥሙ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ለሚያስመጡ አካላት የተለያዩ የማበረታቻ ድጋፎች እያደረገ ነው፡፡" ሲሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስተር ዴኤታ በርኦ ሐሰን ተናግረዋል፡፡
ዴኤታው ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የምታደርገው ሽግግር የሃይል ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ያለመ ስለመሆኑም ገልፀዋል፡፡ ሽግግሩን የሚያሳልጡ በርካታ የታዳሽ ሃይል አማራጮች በበቂ ደረጃ መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የኤሌክትሪክ መኪኖች ሃይል መሙያ ጣቢያዎች እጥረት እና ከከተሞች ውጭ ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ውስንነት እንደ ቀጣይ ተግዳሮቶች መጠቀሳቸውን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ አጋርቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X