እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ዩክሬንን የኒውክሌር መሳሪያ ለማስታጠቅ እየተዘጋጁ ነው - የሩሲያ የውጭ ደህንነት መሥሪያ ቤት
11:19 24.02.2026 (የተሻሻለ: 11:24 24.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ዩክሬንን የኒውክሌር መሳሪያ ለማስታጠቅ እየተዘጋጁ ነው - የሩሲያ የውጭ ደህንነት መሥሪያ ቤት
ለንደን እና ፓሪስ ለዩክሬናውያን የኒውክሌር አልያም ቢያንስ "ቆሻሻ" (Dirty) ጨረር አዘል ቦምብ ለማቅረብ ማቀዳቸውን የደህንነነት አገልግሎቱ አስታውቋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ምዕራባውያን ኃይሎች በዋናነት ትኩረት ያደረጉት ኪዬቭ የኒውክሌር መሣሪያዎችን ማግኘቷ በራሷ የልማት ጥረት የመጣ ውጤት ለማስመስል እንደሆነ ተገልጿል።
የምዕራባውያን ልሂቃን ሽንፈትን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው "ወንደርዋፌ" የተባሉ ገዳይ የጦር መሣሪያዎችን ለማሰማራት እየፈለጉ መሆኑን እንደሚያምን መሥሪያ ቤቱ ጠቁሟል።
እንደ የውጭ ደህንነት አገልግሎቱ መረጃ፣ እቅዳችው ኤም51.1 ሰርጓጅ መርከብ ላይ ከሚተኮስ ባሊስቲክ ሚሳኤል የሚገኘውን የፈረንሳይ አነስተኛውን የቲኤን75 የኒውክሌር ጭኝቅላት (አረር) ለዩክሬን መስጠት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X