የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና የቡሩንዲ ድንበር ከሁለት ወራት መዘጋት በኋላ መከፈቱ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና የቡሩንዲ ድንበር ከሁለት ወራት መዘጋት በኋላ መከፈቱ ተዘገበ
የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና የቡሩንዲ ድንበር ከሁለት ወራት መዘጋት በኋላ መከፈቱ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.02.2026
ሰብስክራይብ

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና የቡሩንዲ ድንበር ከሁለት ወራት መዘጋት በኋላ መከፈቱ ተዘገበ

​ የሁለቱ ሀገራት ባለሥልጣናት በጋቱምባ የድንበር ኬላ በኩል የሚደረገው ድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴ በመደበኛ አሰራር እንዲቀጥል መስማማታቸውን፣ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን የፍልሰት ባለስልጣናትን መግለጫ ጠቅሰው ዘግበዋል።

ባለስልጣናቱ፣ "አሁን ላይ ቡሩንዲ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ በሰላም መሻገር ይችላሉ" ብለዋል።

​ የብሩንዲ ባለስልጣናት የጋቱምባ የድንበር ኬላን የዘጉት ባለፈው ታህሳስ 1 የኤም-23 አማፂያን በምስራቃዊ ኮንጎ የምትገኘውን የኡቪራ ከተማን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ይህም በሁለቱም ወገን ላሉ ማኅበረሰቦች ወሳኝ የሆነውን የንግድ መስመር አስተጓጉሎ ቆይቷል። የኮንጎ ጦር በጥር ወር የኡቪራን ከተማ መልሶ መቆጣጠሩ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና የቡሩንዲ ድንበር ከሁለት ወራት መዘጋት በኋላ መከፈቱ ተዘገበ
የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና የቡሩንዲ ድንበር ከሁለት ወራት መዘጋት በኋላ መከፈቱ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.02.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0