ቻድ ከአማፂያኑ ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት በኋላ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች

ሰብስክራይብ

ቻድ ከአማፂያኑ ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት በኋላ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች

​ የቻድ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ውሳኔው የተላለፈው በሀገሪቱ ላይ የሚፈጸሙ "ተደጋጋሚ ጥቃቶችን" ተከትሎ ሲሆን፣ ዓላማውም የሱዳን ግጭት ወደ ግዛቱ እንዳይዛመት ለመከላከል፣ ዜጎችንና ስደተኞችን ለመጠበቅ እንዲሁም የቻድን መረጋጋትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ እንደሆነ አስታውቋል።

​ሁሉም ቻድን ከሱዳን የሚያገናኙ የድንበር ማቋረጫዎች ለላልተወሰነ ጊዜ ተዘግተዋል፤ ይህም በባለስልጣናት ቅድመ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሰብአዊ ጉዳዮች ውጭ የሰዎችንና የሸቀጦችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ያግዳል።

▪ ይህ እርምጃ የተወሰደው በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል (አርኤስኤፍ) መካከል በሰሜን እና በምዕራብ ዳርፉር ያለው ውጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉ፣ እንዲሁም በቅርቡ አርኤስኤፍ በድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የቻድ ወታደራዊ ካምፖች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ከተሰማ በኋላ ነው።

▪ የሱዳን ባለስልጣናት በቻድ ውሳኔ ላይ እስካሁን የሰጡት አስተያየት የለም።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ በቻድ ጦር እና በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ አማፂያን መካከል የተካሄደ የቅርብ ጊዜ ግጭትን ያሳያል ተብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0