ኢትዮ ቴሌኮም ከ79 ሺህ በላይ ደንበኞቹ አገልግሎቱን ከመዳብ ወደ ፋይበር የመቀየር ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ
13:46 23.02.2026 (የተሻሻለ: 13:54 23.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮ ቴሌኮም ከ79 ሺህ በላይ ደንበኞቹ አገልግሎቱን ከመዳብ ወደ ፋይበር የመቀየር ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ
የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፣ 1.2 ሚሊዮን ደንበኞችን የመሸከም አቅም ያለውና ከፍተኛ ፍጥነት የሚኖረው የኢንተርኔት አገልግሎት ለማቅረብ 14,413 ኪሎ ሜትር የሜትሮ ፋይበር መዘርጋቱን ይፋ አድርገዋል።
ከመዳብ ወደ ፋይበር የሚደረገው ሽግግር ኢትዮ ቴሌኮም ለታማኝ የኢንተርኔት አገልግሎት እየጨመረ የመጣውን ፍላጎት ለማሟላት የያዘው ስትራቴጂ ቁልፍ አካል መሆኑን ፍሬሕይወት አክለው ገልፀዋል።
ኩባንያው፣ “ፋይበር ቱ ዘ ሩም” የተሰኘ አዲስ አገልግሎትም አስተዋውቋል። ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ አማራጭ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት በቀጥታ ደንበኛው ወደሚፈልገው ክፍል የሚያደርስ ነው፡፡
እንደ ክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ዘመናዊ የቤት ውስጥ ሲስተሞች ላሉ የላቁ ቴክኖሎጂዎች አመቺ የሆነ እጅግ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሚያቀርብ ተገልጿል።
ቪዲዮው፦ ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ የዲጂታል ስትሪሚንግ አገልግሎት ይፋ ያደረገበት ሁነትን ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X