በቀጣይ 6 ወራት 1452 የሚደርሱ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመላ ሀገሪቱ ለመገንባት ታቅዷል - የትምህርት ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

በቀጣይ 6 ወራት 1452 የሚደርሱ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመላ ሀገሪቱ ለመገንባት ታቅዷል - የትምህርት ሚኒስቴር

ሚኒስቴሩ፣ እንዳስታወቀው በእቅድ ከተቀመጡት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገሚሱ በሚንስቴሩ ሲገነቡ፣ ቀሪዎቹ በክልሎች አቅም የሚገንቡ ይግባሉ፡፡ ‎ትምህርት ቤቶቹን ለመገንባት ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎችና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ወረዳዎች ልየታ ተድርጓል።

ከዚህ ቀደም፣ ከ34 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ቢገኙም፣ የነበረውን ክፍተት በሚፈለገው ልክ መሙላት ባለመቻሉ በርካታ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገልጿል።

የትምህርት ቤቶቹ የግንባታ ዲዛይን የተዘጋጀ ሲሆን፣ እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መጠነኛ ለውጥ እንዲኖራቸው እንደሚደረግና ለፈጠራ በማነሳሳት ሁለንተናዊ እድገታቸው ላይ አወንታዊ ሚና እንዲኖረው ተደርጎ መዘጋጀቱም ተጠቁሟል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0