የናይል ተፋሰስ ከፍተኛ የመስኖ ልማት አቅም የምግብ ሉዓላዊነትን እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11:16 23.02.2026 (የተሻሻለ: 11:24 23.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናይል ተፋሰስ ከፍተኛ የመስኖ ልማት አቅም የምግብ ሉዓላዊነትን እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ፣ 'የናይል ድምጽ፡ በውሃ አስተዳደር ማኅበረሰቡን በተለይም ወጣቶችና ሴቶችን ማሳተፍ' በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ሱዳን ጁባ በተከበረው የናይል ተፋሰስ ትብብር ቀን ላይ ናይል ቀጣናዊ ትብብርን የማጠናከር ግዙፍ አቅም አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ናይል፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ያለው አቅም የንግድ ግንኙነትን ጨምሮ ቀጣናዊ ትስስርን እንደሚያጠናክር አፅኖት የሰጡት ሚኒስትሩ፣ በተባበረ ክንድ በተፋሰሱ ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አክለውም፣ በቀጣናው በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ድርቅና የጎርፍ አደጋ መቋቋም የሚያስችል አቅም መገንባት ይቻላል ብለዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ጫና በተከሰተበት በአሁኑ ወቅት የግብርናውን የዝናብ ጥገኝነት በመቀነስ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደሚቻል አብራርተዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X