የኢራን እና የአሜሪካ የኒውክሌር ድርድር በመጋቢት አጋማሽ ላይ ይቀጥላል ተባለ

ሰብስክራይብ

የኢራን እና የአሜሪካ የኒውክሌር ድርድር በመጋቢት አጋማሽ ላይ ይቀጥላል ተባለ

​ በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል የሚደረገው አዲስ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ጊዜያዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ ያስችላል ሲሉ አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣን ለምዕራባውያን የዜና ወኪል ተናግረዋል።

​ ሂደቱ በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ በኦማን በተካሄደ ስብሰባ የተጀመረ ሲሆን፣ በወቅቱም የኢራን የኒውክሌር ኃይል ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ መዋሉን የሚያረጋግጥ የወደፊት ስምምነት መሰረታዊ መርሆዎች ተነድፈዋል። ሁለተኛው ዙር ውይይት በየካቲት 10 በጄኔቫ የተካሄደ ሲሆን፣ ቴህራን ዩራኒየምን የማበልጸግ መብቷ እንዲከበር በያዘችው አቋም ፀንታለች።

​ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ትጥቅ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ፣ ካልሆነ ግን ባለፈዉ ዓመት ሰኔ ውስጥ ከተፈጸመው የከፋ ወታደራዊ ጥቃት እንደሚሰነዘር በማስጠንቀቅ የማይለወጥ አቋም ይዘዋል። አሜሪካ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2026 መጀመሪያ ላይ በኦማን ባህረ ሰላጤ እና በፋርስ ባህረ ሰላጤ ያላትን ወታደራዊ ሃይል አጠናክራለች።

​ በቪዲዮው ላይ በጄኔቫ ድርድር ላይ የተሳተፉት የአሜሪካ እና የኢራን ልዑካን የካቲት 10 በኦማን አምባሳደር መኖሪያ ግቢ ውስጥ የተደረገውን ውይይት አጠናቅቀው ሲወጡ ይታያሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0