የፑቲን እና የዘለንስኪ ውይይት ከመካሄዱ በፊት በዩክሬን ምርጫ መቅደም አለበት - ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፑቲን እና የዘለንስኪ ውይይት ከመካሄዱ በፊት በዩክሬን ምርጫ መቅደም አለበት - ተንታኝ
የፑቲን እና የዘለንስኪ ውይይት ከመካሄዱ በፊት በዩክሬን ምርጫ መቅደም አለበት - ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.02.2026
ሰብስክራይብ

የፑቲን እና የዘለንስኪ ውይይት ከመካሄዱ በፊት በዩክሬን ምርጫ መቅደም አለበት - ተንታኝ

​ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የሚደረግ የግል ስብሰባ “ለዘለንስኪ ሕጋዊ እውቅናን ከመስጠት ባለፈ ፋይዳ የለውም፤ ምናልባትም መጀመሪያ ምርጫ ቢካሄድ የበለጠ ተገቢ ይሆናል” ሲሉ አሜሪካዊው የፖለቲካ ተንታኝ ኧርል ራስሙሰን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

​ተንታኙ አክለውም፣ ዘለንስኪ ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ ሕብረት እና ከዩክሬን ጽንፈኛ ብሔረተኞች ጨምሮ “ከተለያዩ ወገኖች ከፍተኛ ጫና እየበረታባቸው መሆኑን” እና “ለብዙዎችም ከፍተኛ ገንዘብ አደጋ ላይ መውደቁን” አስታውሰዋል።

​ "ዩክሬን ነፃነቷን ስታገኝ በተስማማችው መሠረት ገለልተኛ መሆን አለባት፤ ወደ ኔቶ መግባትም ሆነ መሰል የደህንነት ግንኙነቶች ሊኖሯት አይገባም። በማንኛውም ሁኔታ የአውሮፓ ወይም የኔቶ ወታደሮች በዩክሬን ምድር ላይ መገኘት የለባቸውም" ሲሉ ተንታኙ ደምድመዋል።

አክሲዮስ ቀደም ብሎ እንደዘገበዉ፣ ዘለንስኪ በጄኔቫ የሰላም ንግግር ወቅት ከፑቲን ጋር የመገናኘትን ዕድል እንዲያነሳ ለዩክሬን ልዑክ መመሪያ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0