ከ50 በመቶ በታች የነበረው የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ወደ 66.3 በመቶ ማደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ
13:38 22.02.2026 (የተሻሻለ: 13:44 22.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከ50 በመቶ በታች የነበረው የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ወደ 66.3 በመቶ ማደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ
ባለፉት ዓመታት በመንግሥት የተወሰዱ የፖሊሲና የስትራቴጂ ማሻሻያዎች በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ትርጉም ያለው ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋፆ ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገልፀዋል።
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመክፈቻ መርሃ ግብር "ኢትዮጵያ ታምርት አዲስ አበባ ትበልጽግ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬክሽን ማዕከል ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውጭ ንግድ ገቢ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአገር ውስጥ ምርት መተካት ረገድ ከአገር አቀፍ አማካይ ዕድገት በላይ ውጤት እያስመዘገበ እና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል መባሉን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X