ለሶማሊያ የሚሰጠው የምግብ እርዳታ በመጪው ሚያዝያ ሊቆም ይችላል፤ ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ ረሃብ ያጋልጣል - ተመድ
12:18 22.02.2026 (የተሻሻለ: 12:24 22.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ለሶማሊያ የሚሰጠው የምግብ እርዳታ በመጪው ሚያዝያ ሊቆም ይችላል፤ ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ ረሃብ ያጋልጣል - ተመድ
"ሁኔታው በአሳሳቢ ፍጥነት እየተባባሰ ነው" ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም የአደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ ዳይሬክተር ሮስ ስሚዝ ገልጸዋል።
ሶማሊያ ተደጋጋሚ የዝናብ እጥረት ካጋጠማት በኋላ ባለፈው ህዳር ወር ብሔራዊ የድርቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀች ሲሆን፣ አጎራባች አገሮችም ተመሳሳይ ጉዳት አጋጥሟቸዋል። በገንዘብ እጥረት ምክንያት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለ2.2 ሚሊዮን ሰዎች ይሰጥ የነበረውን እርዳታ ከ600,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ብቻ እንዲወሰን አድርጓል። ይህም ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ለሕፃናት የሚሰጠውን የሥርዓተ-ምግብ ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶታል።
ሶማሊያ እ.ኤ.አ. በ2022 ከፍተኛ በሆነ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ረሃብን መከላከል የተቻለበትን መሰል ወሳኝ ወቅት ላይ ትገኛለች ያለው ድርጅቱ፤ ከመጪው መጋቢት እስከ ነሐሴ ወር ድረስ ሥራውን ለመቀጠል 95 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገልጿል።
ስሚዝ አክለውም፣ ይህ የቀነሰው እርዳታ እንኳን ቢቆም የሚያስከትለው ሰብአዊ፣ ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ መዘዝ አስከፊ እንደሚሆንና ከሶማሊያ ድንበር ባለፈም ተፅኖው እንደሚታይ አስጠንቅቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X