የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት በዓል – የ44ኛ ዙር ንጋት ኮርስ የኮማንዶ ሠልጣኞች ተመረቁ
11:00 22.02.2026 (የተሻሻለ: 11:04 22.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት በዓል – የ44ኛ ዙር ንጋት ኮርስ የኮማንዶ ሠልጣኞች ተመረቁ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በሐዋሳ ከተማ በደማቅ ወታደራዊ ሥነ-ስርዓት እያከበረ ይገኛል።
በሥነ–ስርዓቱ ላይ የዕዙ 44ኛ ዙር ንጋት ኮርስ የኮማንዶ ሠልጣኞች ተመርቀዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ለተመራቂዎቹ የቀይ መለዮ የመልበስ ፈቃድ በመስጠት፣ በከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎችም መለዮ አልብሰዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


