በአፍሪካ ቋንቋዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግና ካዛ ባሻገር - የአፍ መፍቻ ቋንቋዎችን የማበልጸግ አስፈላጊነት
10:07 22.02.2026 (የተሻሻለ: 10:14 22.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአፍሪካ ቋንቋዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግና ካዛ ባሻገር - የአፍ መፍቻ ቋንቋዎችን የማበልጸግ አስፈላጊነት
"ልጆች በደንብ በሚረዱት ቋንቋ ሲማሩ በተሻለ ሁኔታ እንደሚገነዘቡ እናውቃለን" ሲሉ በደቡብ አፍሪካ "የሩም ቱ ሪድ" ግብረ-ሰናይ ድርጅት የሊትሬሲ ዳይሬክተር ናዲማ ጆጊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀንን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት፣ በቋንቋ ዙሪያ የኢኮኖሚ ሥርዓቶችን መገንባት "በአሁኑ ወቅት ጥቅም ላይ ያልዋሉ በርካታ የኢኮኖሚ ዘርፎችን" ሊከፍት እንደሚችል ገልጸዋል።
እነዚህም ዘርፎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
🟠 ቋንቋዎችን በምሁራዊ ደረጃ ማሳደግ፣
🟠 ምርምር፣
🟠 የማስተማሪያ ቁሳቁስ ዝግጅት እና
🟠 የትርጉም አገልግሎቶች ይገኙበታል።
የደቡብ አፍሪካን ተሞክሮ ሲያብራሩም፣ ምንም እንኳን ከአፓርታይድ ሥርዓት ጋር የሚያያዝ ቢሆንም፣ አፍሪካንስ ቋንቋ "አንድን ዝቅተኛ ደረጃ የነበረውን ቋንቋ እንዴት ወደ ላቀና ከፍተኛ ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ነው" ብለዋል።
ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ያላቸው "ርዕዮተ-ዓለማዊ አቋም" ደቡብ አፍሪካ በቅኝ አገዛዝ ወቅት የታፈኑ ሌሎች ቋንቋዎቿን በተመሳሳይ መንገድ እንዳታሳድግ እንቅፋት እየሆነ መሆኑን ጠቁመዋል።
ጆጊ አክለውም፣ አንዳንዶች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ድጋፍ የሚያደርጉት እንደ ኢኮኖሚያዊ ኢንቨስትመንት ቢሆንም፣ እሳቸው ግን የዚህ አመክንዮ "ደጋፊ" አለመሆናቸውን ገልጸዋል።
ከኢኮኖሚ ባሻገር ያለውን የሀገሪቱን የቋንቋ ስብጥር እና ብዝሃነት አስፈላጊነትም እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡
"ደቡብ አፍሪካ ውጤታማ ዲሞክራሲ እንዲኖራት የሚቻለው፣ የብዙ ቋንቋዎች ባለቤት መሆኗን ስትቀበል እና እያንዳንዱ ዜጋ ማንነቱን በሚገልጽ መልኩ እንዲሳተፍ ስትፈቅድ ብቻ ነው" ሲሉ ጆጌ አስረድተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X