ደቡብ አፍሪካ በዓለም ኃያላን የባላንጣነት ፉክክር ውስጥ አትገባም ሲሉ ራማፎሳ በብሄራዊ የጦር ኃይሎች ቀን ሰልፍ ላይ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ በዓለም ኃያላን የባላንጣነት ፉክክር ውስጥ አትገባም ሲሉ ራማፎሳ በብሄራዊ የጦር ኃይሎች ቀን ሰልፍ ላይ ተናገሩ

​"የጦር ኃይሎቻችን የተለያየ ማንነትና መነሻ ያላቸውን፣ ነገር ግን በጋራ የሀገር ልጅነትና ዓላማ የተሳሰሩትን የደቡብ አፍሪካ ህዝቦች ብዝሃነት የሚያንፀባርቁ ናቸው። በዴሞክራሲያዊ ሕገ-መንግሥታችን እሴቶች እንዲሁም የሀገራችንን ህዝቦች መሰረታዊ መብቶች በማስከበር ረገድ አንድ ነን፡፡" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ገልጸዋል።

​🪖 ጦር ሜዳው በፍተኛ ቴክኖሎጂ የታገዙ እንደ ድሮን፣ ዲጂታል ውጊያ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወዳሉ ራሳቸውን ችለው ወደሚሰሩ ሥርዓቶች እየተቀየረ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሰራዊት ውስን ሀብቶች ቢኖሩትም ቅልጥፍናውን ጠብቆ ከሁኔታዎች ጋር መላመድ እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

​ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ የጦር ሰራዊት ክፍሎች ፖሊስን በመደገፍ የወንጀለኛ ቡድኖችን እና ሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮን እንዲዋጉ ፈቃድ መስጠታቸውን ገልጸው፤ ይህም የተጋላጭ ማኅበረሰቦችን ደህንነት ለመጠበቅ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

​ ከጎርጎሮሳውያኑ 2017 ጀምሮ መከበር የጀመረው የደቡብ አፍሪካ የጦር ኃይሎች ቀን፣ እ.ኤ.አ. በ1917 በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት "የኤስኤስ ሜንዲ" መርከብ በመስጠሟ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡትን ወታደሮች ለማሰብ ይከበራል። የመርከቧ መስጠም በጦርነቱ ውስጥ ከተመዘገቡት አሳዛኝ ክስተቶች አንዱ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0