አስር የአፍሪካ ሀገራት በዓለም ከቀዳሚ የኢኖቬሽን ሥነ-ምሕዳር ደረጃ ዝርዝሮች ውስጥ ተካተቱ

አስር የአፍሪካ ሀገራት በዓለም ከቀዳሚ የኢኖቬሽን ሥነ-ምሕዳር ደረጃ ዝርዝሮች ውስጥ ተካተቱ
ስታርትአፕ ብሊንክ ባወጣው የ2026 የዓለም አቀፍ የጅማሮ (ስታርትአፕ) ኢኮ-ሲስተም መረጃ መሠረት፣ ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን በዓለም ደረጃ 61ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። የጥናት ተቋሙ ከ125 በላይ ሀገራትን የገመገመው እንደ የሕግ ማዕቀፍ፣ የካፒታል አቅርቦት፣ የግብር ሥርዓት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማት እና ዓለም አቀፍ ተንቀሳቃሽነት ያሉ መስፈርቶችን በመጠቀም ነው።
በጎርጎሮሳዊያኑ 2026 የአፍሪካ ምርጥ 10 የኢኖቬሽን ሥነ-ምሕዳር ያሉባቸው ሀገራት፦
ደቡብ አፍሪካ - ከዓለም 61ኛ (52 ነጥብ)
ኬንያ - ከዓለም 68ኛ (48 ነጥብ)
ኬፕ ቨርዴ - ከዓለም 70ኛ (47 ነጥብ)
ሞሮኮ — ከዓለም 80ኛ (43 ነጥብ)
ኮት ዲቯር — ከዓለም 81ኛ (43 ነጥብ)
ናሚቢያ — ከዓለም 83ኛ (42 ነጥብ)
ቱኒዝያ — ከዓለም 87ኛ (40 ነጥብ)
ሩዋንዳ — ከዓለም 91ኛ (40 ነጥብ)
ግብፅ — ከዓለም 94ኛ (38 ነጥብ)
ናይጄሪያ — ከዓለም 95ኛ (38 ነጥብ)
ሪፖርቱ እንደገለጸው፣ ውጤቱ በአኅጉሪቱ የታየውን ከፍተኛ መሻሻል በተለይም ግልጽ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎች መፈጠርን፣ የተሻለ የካፒታል አቅርቦት እና የላቀ ዓለም አቀፍ ትስስር መኖሩን ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X