የአየር ወለድና የኮማንዶ አባላት በቅንጅት ያሳዩት ልዩ ልዩ ወታደራዊ ክህሎት የሠራዊቱን ከፍተኛ ብቃት ያረጋገጠ ነው - ዐቢይ አሕመድ
18:30 21.02.2026 (የተሻሻለ: 18:34 21.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአየር ወለድና የኮማንዶ አባላት በቅንጅት ያሳዩት ልዩ ልዩ ወታደራዊ ክህሎት የሠራዊቱን ከፍተኛ ብቃት ያረጋገጠ ነው - ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን በማስመልከት በሐዋሳ ከተማ ፍቅር ሐይቅ ላይ የቀረበውን ወታደራዊ ትርዒት አድንቀዋል፡፡
"እዙ አሁን ላይ በመከላከያ ሪፎርም ስራዎች አማካኝነት አየር ወለድ፣ ኮማንዶ እና ልዩ የጸረ ሽብር ኃይል በመያዝ በአደረጃጀት፣ በሠው ኃይል እና በትጥቅ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ተዋቅሮ በየትኛውም ጊዜና በማንኛውም ሁኔታ ግዳጁን በብቃት ለመፈጸም በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ጽፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ በበዓሉ ላይ የቀረበው የተቀናጀ የውሃ ላይ ልምምድ፣ የአየር ወለድና የኮማንዶ አባላት በቅንጅት ያሳዩት ልዩ ልዩ ወታደራዊ ክህሎት የሠራዊቱን ከፍተኛ ብቃት ያረጋገጠ ነው መሆኑን ገልፀዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እዙ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ሲያከብር የገነባውን የዘመነ ወታደራዊ አቅም፣ የሰው ኃይል ዝግጁነት እና የታክቲክ ብቃት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።
የወታደራዊ ልምምድ ትርኢቱን ከቪዲዮው ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X