መራጭ እይታ፦ ዓለም አቀፋዊ ትርክቶች የአፍሪካን ገጽታ እንዴት ያጣምማሉ?

ሰብስክራይብ

መራጭ እይታ፦ ዓለም አቀፋዊ ትርክቶች የአፍሪካን ገጽታ እንዴት ያጣምማሉ?

​“ዓለም አቀፋዊ ትርክቶች አፍሪካን በቀላሉ ችላ አይሏትም። ይልቁንም አሁን ያለውን የኃይል መዋቅር በሚያመች መልኩ የተመረጡ የአፍሪካ ገጽታዎችን ብቻ አውጥተው ያሳያሉ። የሚነገሩት ታሪኮችም ብዙ ጊዜ የውጭ ታዳሚዎችን የሚያጽናኑ እንጂ የአገር ውስጥ ኢ-ፍትሃዊነትን የሚቀይሩ አይደሉም” ሲሉ ራቼል አቲኖ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።

​ የቆየው የአፍሪካውያን የታሪክ አወቃቀር (የታሪክ አነጋገር) ከመዝናኛነት ባለፈ፣ ከቅኝ ግዛት ሥርዓትና ከመደበኛ ተቋማት መፈጠር ከረጅም ጊዜ በፊት ወሳኝ ዕውቀቶችን ለማስተላለፍና ለህልውና እንደ መሠረተ ልማት የሚያገለግል እንደነበር ይሞግታሉ፤ ዛሬ ላይ ይህንን ታላቅ ጥበብ ወደ ተራ ግንኙነት ወይም ግንዛቤ ማስጨበጫነት ማውረድ "ለውጥ ሳይሆን ቆርጦ መጣል ነው" ሲሉም አክለዋል።

አቲኖ፣ የአፍሪካ የታሪክ አወቃቀር እንዲገለል የተደረገው ሆን ተብሎ መሆኑንና ማን መናገር እንዳለበትና ምን መናገር እንዳለበት በሚቆጣጠሩ ተቋማት አማካኝነት እንደሆነም ያስረዳሉ። የአፍሪካ ታሪኮች እንደ ጥሬ ዕቃ ነው የሚታዩት፦ አንትሮፖሎጂስቶች ምስክርነቶችን ይሰበስባሉ፣ ጋዜጠኞች አቀናብረው ወደ ውጭ ያሰራጫሉ፤ ተመራማሪዎች ደግሞ ተደራሽ ባልሆኑ መጽሔቶች ላይ ጥናቶችን ያሳትማሉ።

በሁሉም ሁኔታዎች እሴቱ የሚወሰደው ወደ ሌላ ቦታ ሲሆን፣ ታሪኩን የሰጡ ማህበረሰቦች ግን እውቅናም ሆነ የገንዘብ ጥቅም አያገኙም። "ይህ ታሪክ መናገር ሳይሆን ሀብት ማውጣት ነው" ሲሉ ደምድመዋል።

​ የአፍሪካን ገጽታ በትክክል ለማሳየት ከስሜታዊ አንድነት ይልቅ መዋቅራዊ ትብብር እንደሚያስፈልግ አቲኖ ገልፀዋል። ለዚህም የዲጂታል መድረኮች ለፍትሃዊ ማስተዋወቅና ለገቢ ክፍያ እንዲገደዱ የሚደራደር የደቡባዊው ዓለም ጥምረት እንዲመሰረት ሐሳብ አቅርበዋል። ይህም ታሪኮችን ከመለዋወጥ ባለፈ ትግሎችን የሚያስተሳስር እንዲሆን ይመክራሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0