ሉዓላዊነት ወይስ እጅ መስጠት? አክቲቪስቱ ደቡብ አፍሪካ 'የኢምፔሪያሊስቶች አገልጋይነት' ሚናን ተቃወሙ

ሰብስክራይብ

ሉዓላዊነት ወይስ እጅ መስጠት? አክቲቪስቱ ደቡብ አፍሪካ 'የኢምፔሪያሊስቶች አገልጋይነት' ሚናን ተቃወሙ

​በደቡብ አፍሪካ የፍልስጤም ሶሊዳሪቲ ካምፔይን አስተባባሪ ዩሱፍ ቺክቴ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በንግድ ቀረጥ ሳቢያ በሚሰነዘር "ጉንተላ" ላይ ጠንካራ ተቃውሞ እንዲደረግ አሳስበዋል።

​ አገራዊ ፖሊሲን በባዕዳን ትዕዛዝ ለመምራት የሚደረጉ ሙከራዎችን ውድቅ ያደረጉት አስተባባሪው፣ ለእንዲህ ዓይነቱ ጫና እጅ መስጠት የሉዓላዊነት "የሞት አዋጅ" እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።

​ቺክቴ የአፍሪካ ሕብረት የቀጣናዊ ድንበሮችን አንድነት እንዲያስጠብቅና "ከፋፍለህ ግዛ" የሚሉ ስልቶችን እንዲመክት ጥሪ አቅርበዋል።

​ በአሁኑ ወቅት በሶማሊያ፣ በሱዳን እና በኮንጎ እየታዩ ያሉትን "አሰቃቂ" ግጭቶች በውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት የመጡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አኅጉሪቱ ይህንን በጽኑ ልትቃወም እንደሚገባ አሳስበዋል።

​በመጨረሻም፣ ደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግሥቷን ለማክበርና የአገር ውስጥ መገንጠልን ለመከላከል ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።

​ ደቡብ አፍሪካ ከብሪክስ ጋር አጋርነት በመፍጠር፣ ሁሉንም ያካተተ ማኅበረሰብ መገንባት እንደምትችልና "ለአንድ ወገን የኢምፔሪያሊስት ሥርዓት" አስፈላጊውን ሚዛን መጠበቂያ መሆን እንደምትችል ቺክቴ እምነታቸውን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0