ዚምባብዌ፣ የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ 'ሜድ ኢን ዚም' በሚል ብሔራዊ ምርት መለያ ላይ ትልቅ ተስፋ መጣሏን ፕሬዝዳንቱ ገለጹ

ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ፣ የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ 'ሜድ ኢን ዚም' በሚል ብሔራዊ ምርት መለያ ላይ ትልቅ ተስፋ መጣሏን ፕሬዝዳንቱ ገለጹ

​ የምርት መለያና ስያሜዎች እንዲሁ ለማስመሰል የሚደረጉ ተግባራ ሳይሆኑ ጥራትን፣ የደረጃዎች ተግባራዊነትን እና ብሔራዊ ማንነትን የሚገልጹ መሳሪያዎች መሆናቸውን ኤመርሰን ምናንጋግዋ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ "የሀገራችን የተቀነባበሩ ምግቦች፣ መጠጦች፣ የምህንድስና ውጤቶች፣ የመድኃኒት ምርቶች፣ ብረት እና ሌሎች የማምረቻ ውጤቶች በሁሉም ገበያዎች ላይ የ'ሜድ ኢን ዚምባብዌ' (በዚምባቡዌ የተመረተ) የሚል መለያ ምልክትን ሊይዙ ይገባል" ብለዋል።

​ የዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታዎች የዚምባብዌን አምራቾች ቅልጥፍናንና አርቆ አሳቢነትን እንደሚጠይቁ ያሰጠነቀቁ ሲሆን፣ የንግድ ተቋማት የወጪ ንግድ ስልታቸውን በመላው አፍሪካ እና በደቡባዊው የዓለም ክፍል ካሉ አዳዲስ እድሎች ጋር ማጣጣም እንዳለባቸው አስረድተዋል።

​"ያስቀመጥነውን ግብ ለማሳካት ሁሉም ሰው የበኩሉን መወጣት አለበት" ሲሉ ምናንጋግዋ አሳስበዋል።

​ ይህ ተነሳሽነት የመጣው ዚምባብዌ የ'ራዕይ 2030' የልማት አጀንዳን በመከተል በዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ የኢንዱስትሪ መስፋፋትን፣ የጥሬ ዕቃዎች ማቀነባበሪያን እና የእሴት መጨመር ሥራዎችን እያፋጠነች ባለችበት ወቅት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0