'የኢትዮጵያ ታምርት' ሩጫን ዓለማቀፋዊ ይዘት የሚያሰጥ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
13:03 21.02.2026 (የተሻሻለ: 13:14 21.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
'የኢትዮጵያ ታምርት' ሩጫን ዓለማቀፋዊ ይዘት የሚያሰጥ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
የጋራ መግባቢያ ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን በመወከል'የኢትዮጵያ ታምርት' ሩጫ አስተባባሪ አብዱልፈታ የሱፍ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አትሌት ስልሽ ስህን ተፈራርመዋል።
የስምምነቱ ዓላማ የኢትዮጵያ ታምርት ሩጫን ዓለማቀፋዊ ደረጃን (ስታንዳርድ) ያሟላ በማድረግ ለአትሌቶች የስኬት አንዱ መንገድ እንዲሆን ለማስቻልና የሌሎች ዓለም ሀገራት ታዋቂና አዳዲስ አትሌቶችን ያካተተ ሆኖ እንዲቀጥል ጉልህ ሚና እንዲኖረው ማስቻል ነው፡፡
4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ሩጫ ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት በሚል መሪ ቃል በመጪው ሚያዚያ 18 ይካሄዳል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ቪዲዮ፡- ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ሩጫ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X