ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ የዲጂታል ስትሪሚንግ አገልግሎት አስጀመረ
21:23 20.02.2026 (የተሻሻለ: 07:34 21.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ የዲጂታል ስትሪሚንግ አገልግሎት አስጀመረ
አገልግሎቱ ይዘት ፈጣሪዎች፣ ፕሮዲዩሰሮች፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች ጭምር የፈጠራ ሥራዎቻቸውን በቴሌ ብር ተደራሽ የሚያደርጉበት አዲስ ዲጂታል አማራጭ ነው ተብሏል።
ከመዝናኛና የፈጠራ ሥራዎች ባለፈ ትምህርት ነክ ይዘቶች በመላ ሀገሪቱ 24/7 ተደራሽ የሚሆኑበት 'ናሽናል ዲጂታል ኮንቴንት ፕላትፎርም' እንደሆነም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።
“ፕሮዲዩሰሮች፣ ሚዲያዎች፣ ይዘት ፈጣሪዎች ሥራዎቻቸውን ይዘው ይመጣሉ እኛም በቴሌብር አገልግሎት ለተጠቃሚዎች እናደርሳለን፤ ክፍያውም በቴሌ ብር ይፈጸማል” ብለዋል።
ለስርጭት አገልግሎቱ የሚሆኑ 10 ሺህ ገደማ በሲም ካርድ የሚሠሩ አነስተኛ ማሠራጫ ዲኮደሮች በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ መቅረባቸውንም አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X