የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ልጅ በሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው
19:55 20.02.2026 (የተሻሻለ: 20:04 20.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ልጅ በሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው
ቻቱንጋ ሙጋቤ እና ግብረ አበሩ፤ በጆሃንስበርግ በሚገኘው የሙጋቤ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከተፈጸመ ተኩስ ጋር በተያያዘ በሰው መግደል ሙከራ ወንጀል በአሌክሳንድራ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሏል።
በጋውቴንግ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አገልግሎት፤ ሁለቱ ግለሰቦች መጀመሪያ ለጥያቄ ተጠርተው እንደነበር እና አሁን ግን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ገልጿል። ፖሊስ በድርጊቱ አንድ የ23 ዓመት ወጣት በጥይት ተመትቶ ለሕይወቱ አደገኛ የሆነ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል ብሏል።
ወንጀሉ በተፈጸመበት ቦት የተተኮሱ የቀለሃ ቀፎዎች ቢገኙም ለተኩሱ ጥቅም ላይ የዋለው ሽጉጥ ግን እስካሁን አልተገኘም።
ተጎጂው በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የሚሠራ አትክልተኛ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሕክምና ላይ ይገኛል። ጥቃቱ ለምን እንደተፈጸም እስካሁን በግልጽ አይታወቅም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X