የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራምፕን ‘የአስቸኳይ ጊዜ ታሪፍ’ ውሳኔ አገደ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራምፕን ‘የአስቸኳይ ጊዜ ታሪፍ’ ውሳኔ አገደ
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራምፕን ‘የአስቸኳይ ጊዜ ታሪፍ’ ውሳኔ አገደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.02.2026
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራምፕን ‘የአስቸኳይ ጊዜ ታሪፍ’ ውሳኔ አገደ

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፤ ዶናልድ ትራምፕ ዓለም አቀፍ የአስቸኳይ ጊዜ የኢኮኖሚ ሥልጣን ሕግን ተገን አድርገው የጣሉት ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ ከፕሬዚዳንቱ ሥልጣን በላይ መሆኑን በመግለጽ ስድስት ለሦስት በሆነ አብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል።

ዋና ዳኛ ጆን ሮበርትስ በጻፉት የውሳኔ ሐሳብ፤ ፕሬዚዳንቱ "የመጠን፣ የጊዜ እና የወሰን ገደብ የሌለው ታሪፍ የመጣል ልዩ ሥልጣን አለኝ" ማለታቸው አግባብ እንዳልሆነና እንዲህ ዓይነት እርምጃዎችን ለመውሰድ ከኮንግረሱ ግልጽ ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ፍርድ ቤቱ በሕጉ መሠረት ቀረጥ የመጣልና የመሰብሰብ ሥልጣን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ (ኮንግረስ) እንጂ የፕሬዚዳንቱ እንዳልሆነ በድጋሚ አረጋግጧል።

የተቃውሞ ውሳኔው የአሜሪካ መንግሥት እስካሁን በሕገ-ወጥ ታሪፍ የሰበሰበውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዲመልስ ሊገደድ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0