የደቡብ አፍሪካ የፍሪጅ አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ ፋብሪካ ሊያቋቁም ነው
18:33 20.02.2026 (የተሻሻለ: 18:34 20.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ የፍሪጅ አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ ፋብሪካ ሊያቋቁም ነው
በፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ካደረገው ጌሊዶ ከተባለ የፍሪጅ አምራች ኩባንያ ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የዘርፉ የኢንቨስትመንት ዕድል ላይ ውይይት ማድረጉን አስታውቋል።
የኤምባሲው ተወካዮች ለኩባንያው አመራሮች በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ፣ መንግሥት ለአምራች ዘርፉ ስለሚሰጠው ቅድሚያ እንዲሁም ስላለው ሰፊ የገበያ ዕድል ገለጻ አድርገዋል።
የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ሮበርት ሃትሚል፤ በኢትዮጵያ የሚያቋቋመው ፋብሪካ በዓመት 300 ሺህ ፍሪጆችን የማምረት አቅም እና በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ከ700 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ባቀረቡት ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ ጠቅሰዋል።
ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባቱ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የውጭ ምንዛሬን በማመንጨት ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ታምኖበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X