የደቡብ አፍሪካ ወታደራዊ የጤና አገልግሎት ነፃ የሕክምና ድጋፍ እየሰጠ ነው
18:05 20.02.2026 (የተሻሻለ: 18:14 20.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ወታደራዊ የጤና አገልግሎት ነፃ የሕክምና ድጋፍ እየሰጠ ነው
የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል በሊምፖፖ ግዛት የሚያከናውነውን የ "ኦዌቱ ፕሮጀክት" አካል በማድረግ፤ ወታደራዊ ሐኪሞች እና የአይን ስፔሻሊስቶች በኤሊም ሆስፒታል የአይን ምርመራ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ህክምና በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
በዚህ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት፤ ቅድመ መከላከል በማድረግ መዳን በሚችሉ ምክንያቶች አይነ ስውር ለሆኑ ታካሚዎች ብርሃን እየመለሱ ይገኛል።
ይህ ተነሳሽነት በገጠራማ አካባቢዎች ለሚገኙና የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ለሚቸገሩ ማህበረሰቦች የጤና እንክብካቤ፣ ማህበራዊ ድጋፍ እና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የተዘረጋ ሰፊ ፕሮግራም አካል ነው።
የጦር ኃይሎችን ቀን ምክንያት በማድረግ የሚከናወነው "ኦዌቱ ፕሮጀክት" እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ የገጠር ነዋሪዎችን ሕይወት መለወጥ ችሏል።
በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል የቀረበ ተንቀሳቃሽ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X