ኢትዮጵያ ከሥጋ የወጪ ንግድ በስድስት ወራት ውስጥ 61.76 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከሥጋ የወጪ ንግድ በስድስት ወራት ውስጥ 61
ኢትዮጵያ ከሥጋ የወጪ ንግድ በስድስት ወራት ውስጥ 61 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.02.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከሥጋ የወጪ ንግድ በስድስት ወራት ውስጥ 61.76 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

በግማሽ ዓመቱ 10,655 ቶን የፍየል፣ በግ፣ በሬ፣ ግመል እና የዕርድ ተረፈ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ገቢው መገኘቱን የኢትዮጵያ የእንስሳት ልማት ኢንትቲትዩት አስታውቋል።

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ15 በመቶ ብልጫ እንዳለው የኢንስቲትዩቱን ኃላፊ ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኳታር፣ ኩዌት፣ ዮርዳኖስ፣ ባህሬን እና ኦማን ለኢትዮጵያ ስጋና የተረፈ ምርቶች ዋነኛ ገበያ መዳረሻ እንደሆኑ ተገልጿል።

የሥጋና ተዋጽኦ ምርቶችን በጥራት አዘጋጅቶ መላክ የሚያስችሉ 12 የኤክስፖርት ቄራዎች ሥራ ላይ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0