በወላይታ ዞን 81 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ
15:33 20.02.2026 (የተሻሻለ: 15:44 20.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በወላይታ ዞን 81 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ
ይህ የማዕድን ክምችት መጠን በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ በ81 ካሬ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ እንደሚገኝ ባካሄደው ጥናትና ምርምር ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የተገኘው የድንጋይ ከሰል፤ ለሲሚንቶ ማምረቻ፣ ለኢንዱስትሪ ቦይለሮች እና ለጡብ ፋብሪካዎች እንደ ዋነኛ የኃይል ምንጭነት ማገልገል እንደሚችል ተጠቁሟል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በኦሞ ተፋሰስ የተገኘው ይህ የድንጋይ ከሰል ክምችት ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ መስፋፋት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሏል።
ኢትዮጵያ ለድንጋይ ከሰል ግዢ በየዓመቱ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ እንደምታወጣ የማዕድን ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X