የኢትዮጵያን ሀገር በቀል ዕውቀቶች የመለየትና የመሰነድ ሥራ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተጀምሯል - ትምህርት ሚኒስቴር
17:48 19.02.2026 (የተሻሻለ: 18:44 19.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያን ሀገር በቀል ዕውቀቶች የመለየትና የመሰነድ ሥራ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተጀምሯል - ትምህርት ሚኒስቴር
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሀገሪቱን ጥንታዊና ጠቃሚ ዕውቀቶች ለይቶ ለትውልድ ለማስተላለፍና ለልማት ለማዋል በትኩረት እየሠራሁ ነው ብሏል።
ለዚህም ከ40 በላይ የሀገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማኅበረሰቡን ችግሮች በመፍታትና ባሕላዊ እሴቶችን በማሳደግ ረገድ ወሳኝ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ በሚኒስቴሩ የምርምርና የማኅበረሰብ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰራዊት ሐምዲሶ (ዶ/ር) ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል።
ይህ አቅጣጫ የሀገርን ተወዳዳሪነትና ውስጣዊ አቅም ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X