ኢትዮጵያ በዓመት ለድንጋይ ከሰል ግዢ የምታወጣውን ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል የተባለ ፋብሪካ ከፈተች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በዓመት ለድንጋይ ከሰል ግዢ የምታወጣውን ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል የተባለ ፋብሪካ ከፈተች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ የሚገኘውን የአርጆ የድንጋይ ከሰል ማቀነባበሪያ ፋብሪካን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

"የአርጆ ከሰል ድንጋይ መፍጫ ፋብሪካ፤ ከውጭ ሲገባ የነበረውን የተፈጨ ድንጋይ ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላት በኢትዮጵያ የዘርፉ የኢንደስትሪ ልማት ዐቢይ ሚና ይጫወታል። ፋብሪካው ለሲሚንቶ፣ ለብረት እና ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪዎች አስፈላጊ ጥሬ ግብዓቶችን ያቀርባል” ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ሀብታሙ ተገኘ በበኩላቸው፤ በኢትዮጽያ በዓመት እስከ 2.3 ሚሊዮን ቶን የሚደርሰውን የድንጋይ ከሰል ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት ሙሉ በሙሉ እንደሚተካ ገልጸዋል።

ፋብሪካው በሰዓት 200 ቶን በዓመት ደግሞ 1.2 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል የማጠብ አቅም ያለው ሲሆን አንድ ቢሊዮን ብር የሚሆን ገንዘብ ኢንቨስት ተደረጎበት በአንድ ዓመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንደተጠናቀቀ ከማዕድን ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0