ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምዕራብ ወለጋ የቱሉ ካፒ ወርቅ ልማት ፕሮጀክት ግንባታን ጎበኙ

ሰብስክራይብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምዕራብ ወለጋ የቱሉ ካፒ ወርቅ ልማት ፕሮጀክት ግንባታን ጎበኙ

“የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብት ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት እንዴት መጠቀም እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ” ሲሉ ጉብኝታቸውን አስመልክቶ ባጋሩት የማኅበራዊ ገጽ መልዕክት ፕሮጀክቱን ገልጸውታል።

በመንግሥት እና በግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተገነባ የሚገኘው የቱሉ ካፒ ወርቅ ልማት ፕሮጀክት፤ ከወርቅ ማውጣት ሥራው ጎን ለጎን ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ለሚያደርጉ የጤና፣ የመንገድ ልማት እና የዘመናዊ መኖሪያ ቤት ግንባታዎች ጠቃሚ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ገና ያለተነካ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ያላት ሲሆን ባለፈው በጀት ዓመት መጨረሻ ከወርቅ ሽያጭ ገቢ 275.2 ቢሊዮን ብር ማግኘቷ የሚታወስ ነው፡፡ ይህም በ2016 ዓ.ም ከተመዘገበው 5 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍተኛ ልዩነት የታየበት ነው፡፡

በቅርቡ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ ያደረጉት ናይጄሪያዊው የፖሊሲ አማካሪ ኦቪግዌ ኢጉዌጉ፤ የአፍሪካ ሀገራት በአሜሪካ ዶላር ላይ ካላቸው ከፍተኛ ጥገኝነት ወጥተው የገንዘብ ሉዓላዊነታቸውን ለማረጋገጥ ወርቅን እንደ ዋስትና እንዲጠቀሙ ምክረ ሀሳብ አስቀምጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0