ጋቦን የማኅበራዊ ሚዲያዎችን ላልተወሰነ ግዜ አገደች
18:37 18.02.2026 (የተሻሻለ: 18:44 18.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጋቦን የማኅበራዊ ሚዲያዎችን ላልተወሰነ ግዜ አገደች
የሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን የ "ሕገ-ወጥ ይዘቶች ስርጭት" ለእገዳው ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል።
◻ ባለሥልጣኑ በሰጠው ማብራሪያ አንዳንዶች የዲጂታል መድረኮችን በመጠቀም የመንግሥት ተቋማትን፣ የዜጎችን እና የታዋቂ ግለሰቦችን ስም የሚያጠፉ ይዘቶችን እያሰራጩ ይገኛሉ ብሏል።
◻ በተጨማሪም ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሕዝብን ሰላም የሚያውኩ እና የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለማሰራጨት እየዋሉ እንደሆነ ገልጿል።
◻ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣኑ አክሎም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎቹ ራሳቸው የሚለቀቁ ይዘቶችን በአግባቡ አለመቆጣጠራቸው በእጅጉ እንዳሳዘነው አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X