መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት በሁለት ሳምንታት ውስጥ የሙከራ ትግበራ እንደሚጀመር ተገለፀ
18:16 18.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 18.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት በሁለት ሳምንታት ውስጥ የሙከራ ትግበራ እንደሚጀመር ተገለፀ
ይህ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ለመጀምሪያ ግዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስታውቋል።
የአገልግሎቱ ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ማሞ፤ ለሁሉም ማኅበረሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልፀዋል፡፡
የመሠረተ ልማት ተደራሽነት ዝቅተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ‘በኪዮስክ’ አገልግሎት ለመስጠት ጥናት እየተካሄደ መሆኑንም ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በ23 ተቋምት 187 የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተር ጄነራሉ፤ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተቋማትን ወደ 25 በማሳደግ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ 250 አገልግሎቶችን ለመስጠት መታቀዱን ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X