የኤፕስቲን ሰነዶች በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎችን አጋልጠዋል - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኤፕስቲን ሰነዶች በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎችን አጋልጠዋል - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎች
የኤፕስቲን ሰነዶች በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎችን አጋልጠዋል - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.02.2026
ሰብስክራይብ

የኤፕስቲን ሰነዶች በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎችን አጋልጠዋል - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎች

ከጄፍሪ ኤፕስቲን ጋር የተያያዙ በሴቶች እና በሴት ልጆች ላይ የተፈጸሙት ግፎች፤ በመጠናቸው እና ስልታዊነቸው “በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች” የሚለውን የዓለም አቀፍ ሕግ መለኪያ ሊያሟሉ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ገልፀዋል።

እነዚህ ድርጊቶች የጾታ ባርነት፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ ሰዎችን አፍኖ መሰወር፣ ማሰቃየት፣ ሰብዓዊነት የጎደለው አያያዝ እና የሴቶች ግድያን እንደሚያካትቱ ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።

ባለሙያዎቹ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድና የወንጀል ተጠያቂነት እንዲኖር በመጠየቅ፤ ከሥራ መልቀቅ ብቻ በቂ እንዳልሆነ አሳስበዋል።

የአሜሪካ የፍትሕ ሚኒስቴር ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰነዶችን በጥር ወር መጨረሻ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ኤፕስቲን በወሲብ ንግድ ዝውውር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ችሎት እየጠበቀ ባለበት ወቅት በ2019 ወህኒ ቤት ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0