ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ዓለም አቀፍ የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ዓለም አቀፍ የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው

ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ለሲኒማ ጥበብ ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ በ76ኛው የበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል "የበርሊን ካሜራ" የክብር ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።

ሽልማቱ ትናንት የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በዴልፊ ፊልም ፓላስት በተካሄደ ልዩ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተበርክቶላቸዋል።

በዕለቱ የኃይሌ ገሪማ አዲስ ሥራ የሆነውና ወደ ዘጠኝ ሰዓታት ገደማ የሚፈጀው ጥቁር አንበሶች - የሮማ ተኩላዎች ("Black Lions – Roman Wolves") የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለተመልካች ቀርቧል።

ዘጋቢ ፊልሙ የጣሊያን ወረራን ታሪክና አፈ ታሪክ የሚመረምር እንዲሁም የኢትዮጵያውያንን የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ተጋድሎ የሚዘክር ነው።

ምሥል 1 የ Black Lions – Roman Wolves ዘጋቢ ፊልም የጨረፍታ ትዕይንቶችን ያሳያል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ዓለም አቀፍ የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው
ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ዓለም አቀፍ የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.02.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0