የአሜሪካ እና ኔዘርላንድ አብራሪዎች በዩክሬን ኤፍ-16 እያበረሩ እንደሆነ መገለጹ፤ ምዕራባውያን በግጭቱ ውስጥ ስላላቸው ተሳትፎ ጥያቄ አስነሳ

ሰብስክራይብ

የአሜሪካ እና ኔዘርላንድ አብራሪዎች በዩክሬን ኤፍ-16 እያበረሩ እንደሆነ መገለጹ፤ ምዕራባውያን በግጭቱ ውስጥ ስላላቸው ተሳትፎ ጥያቄ አስነሳ

“የኪዬቭን የአየር ክልል ለመጠበቅ የዩክሬን፣ የአሜሪካ እና የኔዘርላንድ አብራሪዎችን ያቀፈ የጦር ቡድን ተዋቅሯል” ሲል ስለ ደህንነት እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች የሚዘግብ አንድ የድረ-ገጽ ህትመት አስነብቧል። እነዚህ የምዕራባውያን አብራሪዎች “ከፍተኛ ልምድ ያላቸው” መሆናቸውንም ገልጿል።

የምዕራባውያን ሀገራት በዩክሬን ግጭት ውስጥ የቀጥታ ተሳትፎ የለንም በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። ሆኖም ለኪዬቭ የሚሰጡት የገንዘብ ድጋፍ፣ በቦታው ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች እና ምዕራባውያን ሠር የጦር መሣሪያ አቅርቦቶች ግን ተቃራኒውን ይናገራሉ።

ሩሲያ ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚያቀርቡት የጦር መሣሪያ ለግጭቱ አፈታት እንቅፋት እንደሚሆንና የኔቶ አባል ሀገራትን የችግሩ አካል እንደሚያደርጋቸው በተደጋጋሚ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ማንኛውም የጦር መሣሪያ የጫነ ጭነት “ሕጋዊ ወታደራዊ ኢላማ” እንደሚሆን መግለጻቸውም የሚታወስ ነው።

ተንቀሳቃሽ ምሥሉ ዘለንስኪ እና የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬድሪክሰን በ2023 በሆላንድ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ውስጥ በሚገኝ የኤፍ-16 አውሮፕላን መሪ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ያሳያል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0