ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን ዕድገት እያሳዩ ካሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች
19:27 17.02.2026 (የተሻሻለ: 19:34 17.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን ዕድገት እያሳዩ ካሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች
የተባበሩት መንግሥታት የቱሪዝም ድርጅት ባወጣው መረጃ መሠረት፤ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 የጎብኚዎች ቁጥርን በ15 በመቶ በመጨመር ከፍተኛ ዕድገት ካስመዘገቡ ሀገራት አንዷ ሆናለች።
ለቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት ምክንያቶች
ሠላምና መረጋጋት፦ በሰሜን ኢትዮጵያ ከነበረው ግጭት በኋላ ሰላም በመስፈኑ እና ወደ ሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉ በረራዎች በ2023 እንደገና መጀመራቸው፣
ኢትዮጵያን ይጎብኙ (Visit Ethiopia)፦ በ2025 ሥራ የጀመረው ይህ የዲጂታል መድረክ ጎብኚዎች በቀላሉ መረጃ እንዲያገኙና የጉዞ ቦታዎችን እንዲይዙ ማድረጉ፣
ተመራጭ መዳረሻዎች፦ የአክሱም ሥልጣኔ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር ፋሲለደስ ግንብ፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እና የኦሞ ሸለቆ የባሕል ቅርሶች ዋነኛ የቱሪስቶች መዳረሻ ሆነው መቀጠላቸው።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ 8 በመቶ የቱሪዝም ዕድገት እንድታስመዘግብ አስችሏታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X