በጄኔቫ ስለተጀመረው የሦስትዮሽ የዩክሬን የሰላም ንግግር እስካሁን የታወቁ መረጃዎች

በጄኔቫ ስለተጀመረው የሦስትዮሽ የዩክሬን የሰላም ንግግር እስካሁን የታወቁ መረጃዎች
◻ ምክክሩ ለሚዲያ ዝግ ሆኖ የሚካሄድ ሲሆን ለሁለት ቀናት ይቆያል። እንደ ክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ገለጻ፤ እስከ ማክሰኞ መገባደጃ ድረስ ምንም ዓይነት ዝርዝር መረጃ አይጠበቅም።
◻ የሩሲያ ልዑካን ቡድን በፕሬዚዳንቱ ረዳት ሜዲንስኪ የሚመራ ሲሆን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋሉዚን፣ የወታደራዊ ደህንነት ኃላፊ ኮስቲዩኮቭ እና ሌሎች ባለሥልጣናትን ያካተተ ነው።
◻ እንደ ፔስኮቭ ገለጻ፤ ንግግሩ የግዛት ጥያቄዎችን ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።
◻ የዩክሬን የደህንነት እና መከላከያ ምክር ቤት ጸሐፊ ኡሜሮቭ እንደገለጹት፤ አጀንዳው የደህንነት እና ሰብዓዊ ጉዳዮችን ያካትታል።
◻ ኡሜሮቭ ቀደም ሲል ኪዬቭ በጄኔቫው ስብሰባ ላይ የ "ኢነርጂ ተኩስ አቁም" ሃሳብ እንደምታነሳ ተናግረው ነበር።
◻ የእንግሊዝ ልዑካን ቡድን በስብሰባው ቦታ አቅራቢያ የታየ ሲሆን የስፑትኒክ ምንጭ ልዑኩ ስለ ንግግሩ ውጤት መረጃ ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
◻ የእንግሊዝ ልዑካን ቡድንን የሚመሩት የስታርመር የደህንነት አማካሪ፤ በጄኔቫ ከአሜሪካ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ቀደም ብለው ስብሰባ አካሂደዋል።
◻ ንግግሩ በሩሲያኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች እየተካሄደ ይገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X