የሩሲያ የቲያትር ጥበባት ኢንስትቲዩት የቲያትር ልህቀት ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ የቲያትር ጥበባት ኢንስትቲዩት የቲያትር ልህቀት ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
የሩሲያ የቲያትር ጥበባት ኢንስትቲዩት የቲያትር ልህቀት ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.02.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የቲያትር ጥበባት ኢንስትቲዩት የቲያትር ልህቀት ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

መርኃ-ግብሩ ታዋቂ የቲያትር ጥበባት ምሁራን፣ ከያንያን፣ ታዋቂ የፊልም ባለሙያዎች እና ጸሐፍያነ ተውኔት በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የቲያትር ልህቀት ሳምንቱን በንግግር የከፈቱት በአዲስ አበባ የሩሲያ የሳይንስ እና የባሕል ማዕከል ኃላፊ ቭላዲሚር ጎሎቫቼቭ፤ ሩሲያና ኢትዮጵያ በበርካታ መስኮች የቆዬ ጠንካራ ትስስር እንዳላቸው ጠቅሰው፤ ዝግጅቱ በባሕል እና በኪነ-ጥበብ ዘርፎች ትብብራቸውን ማጠናከር እንዲችሉ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባሕል ማዕከል አርቲስቲክ ዳይሬክተር ቢኒያም ብርሃኑ በበኩላቸው፤ የቲያትር ልህቀት ሳምንቱ አካል የሆነ የቲያትር ጥበባት ሥልጠና ለአንድ ሳምንት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

የሩሲያ የቲያትር ጥበባት ኢንስትቲዩት መምህር እና ተመራማሪ አሌክሳንደር ባርማክ በበኩላቸው፤ የተቋማቸው መምህራን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ መሠረታዊ እና ጠቃሚ የሆኑ የቲያትር ክህሎቶችን ለማካፈል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው እና የሩሲያ የቲያትር ጥበባት ኢንስትቲዩት ምሁራን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል ሥልጠና በሚሰጡበት በዚህ መርኃ-ግብር፤ ኢትዮጵያውያን የቲያትር ተማሪዎች እና መምህራን አዲስ እና ልዩ ክህሎት የሚገበዩበት እንደሚሆን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የሩሲያ የቲያትር ጥበባት ኢንስትቲዩት የቲያትር ልህቀት ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የሩሲያ የቲያትር ጥበባት ኢንስትቲዩት የቲያትር ልህቀት ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0