35 ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን በይፋ ገልጸዋል - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ሰብስክራይብ

35 ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን በይፋ ገልጸዋል - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው "አየር መንገዱ ለወራት ከተቀዳሚ ዓለም አቀፍ ተቋራጮች ጋር ምክክር ሲያደርግ ቆይቷል። በቴክኒክ ረገድ ብቁ የሆኑ ኩባንያዎች ዝርዝር በ10 ቀናት ውስጥ ተለይቶ የሚታወቅ ሲሆን ጨረታውም ወዲያውኑ ይከተላል" ማለታቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የፕሮጀክቱ የግዜ ሰሌዳ፤ እስከ የካቲት 21 ዝርዝር የንድፍ ሥራዎች እንደሚጠናቀቁ፣ የካቲት 24 ጨረታ እንደሚወጣና ነሐሴ ወር ላይ ከአራት የተመረጡ ኩባንያዎች ጋር የግንባታ ውል እንደሚፈረም ያሳያል ሲል ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

ከላይ በተያያዘው ምሥል እንደሚታየው የመሬት ማጽዳትና የማስተካከል ሥራ እየተፋጠነ ይገኛል።

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ጥር 2 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መጣሉ የሚታወስ ነው።

ከማኅበራዊ ገፅ የተገኘ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0