በቡርኪና ፋሶ እና በኮትዲቯር መካከል አገልግሎት የሚሰጡ አራት አዳዲስ ዘመናዊ ባቡሮች ሥራ ሊጀምሩ ነው
15:02 17.02.2026 (የተሻሻለ: 16:44 17.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በቡርኪና ፋሶ እና በኮትዲቯር መካከል አገልግሎት የሚሰጡ አራት አዳዲስ ዘመናዊ ባቡሮች ሥራ ሊጀምሩ ነው
የቡርኪና ፋሶ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ሚካኢሉ ሲዲቤ፤ በአዳዲስ ሞተሮቹ የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን የሚኒስቴሩ መግለጫ አመልክቷል።
እያንዳንዳቸው የጂኤል 30 የባቡር ተሳቢዎች 3ሺህ የፈረስ ጉልበት አቅም ያላቸው ሲሆን የዲጂታል ቁጥጥር ሥርዓቶች፣ የውስጥ ምርመራ እና የተሻሻሉ የደህንነት መሣሪያዎች የተገጠሙላቸው ናቸው።
የእነዚህ ሞተሮች የግዢ ዋጋ ወደ 7 ቢሊዮን የሲ.ኤፍ.ኤ ፍራንክ (12.6 ሚሊዮን ዶላር) አካባቢ እንደሚገመት ተገልጿል።
አዲሶቹ ባቡሮች በመላው የአቢጃን-ዋጋዱጉ ኮሪደር መስመር አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X