#viral| በ73 ዓመታቸው 102 ልጆች እና 578 የልጅ ልጆች ያፈሩት አባት

ሰብስክራይብ

#viral| በ73 ዓመታቸው 102 ልጆች እና 578 የልጅ ልጆች ያፈሩት አባት

‍‍ በአፍሪካ ምናልባትም ቀዳሚ ወላድ አባት ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚገመቱት የ73 ዓመቱ ኡጋንዳዊ ሙሳ ሃሳህያ ካሴራ፤ ከ12 ሚስቶቻቸው፣ ከ98 ልጆቻቸው (ከወለዷቸው 102 ልጆች መካከል አራቱ በሕይወት የሉም) እና ከ578 የልጅ ልጆቻቸው ጋር በአንድ ጣራ ሥር ይኖራሉ። ሰፊ ቤተሰባቸውን ለመከታተል ስማቸውን የሚመዝግቡበት ልዩ ማስታወሻ ደብተር ይጠቀማሉ።

ካሴራ ቀደም ሲል ሰፊ የእርሻ መሬት የነበራቸው ቢሆንም ወንድ ልጆቻቸው አድገው ትዳር ሲመሰርቱ መሬቱን እያከፋፈሉ ሰጥተዋቸዋል። በገንዘብ እጥረት ምክንያት አንዳንድ ልጆቻቸው ትምህርት ለማቋረጥ ቢገደዱም አብዛኞቹ ግን አሁንም ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

በትልቅ ቤተሰባቸው ደስተኛ ቢሆኑም አሁን ላይ የገንዘብ አቅማቸው ቢሻሻል እንኳ ተጨማሪ ልጅ የመውለድ ፍላጎት የላቸውም። ይልቁንም ትኩረታቸው ልጆቻቸው የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።

አባወራው ለትምህርት ትልቅ ቦታ የሚሰጡ እና የልጅ ልጆቻቸው የተሻለ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ የሚመኙ ናቸው፡፡ ልጆቻቸው ግን በተገቢው ሁኔታ ማስተዳደር እንዲችሉ አነስተኛ ቤተሰብ መመስረት እንዳለባቸው ይመክራሉ።

የእኚህን ሰው ታሪክ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል በኡጋንዳዊ ጦማሪ ከተጋራ በኋላ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጋ እይታ አግኝቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0