በናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለው የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሥራ ማቆም አድማ ለመንገደኞች እንግልት መፍጠሩ ተገለፀ

ሰብስክራይብ

በናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለው የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሥራ ማቆም አድማ ለመንገደኞች እንግልት መፍጠሩ ተገለፀ

በናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኬንያ አቪዬሽን ሠራተኞች ማኅበር የተጀመረው የሥራ ማቆም አድማ፤ አገልግሎት በማስተጓጎሉ በርካታ መንገደኞች ለሰዓታት በአውሮፕላን ማረፊያው እንዲቆዩ መገደዳቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በርካታ አየር መንገዶች የበረራ መዘግየቶች ሲያጋጥማቸው፣ አንዳንድ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን ሌሎች አየር መንገዶች ደግሞ መንገደኞቻቸው ማስታወቂያ እስከሚወጣ ድረስ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እንዳይሄዱ አሳስበዋል።

የሠራተኞች ማኅበሩ በፍርድ ቤት ቢከለከልም የጋራ ድርድር ውይይቶች አለመቋጨታቸውን እና ለቋሚ የሥራ መደቦች ጊዜያዊ የቅጥር ውል ጥቅም ላይ መዋሉን በመጥቀስ የሥራ ማቆም አድማውን ሰኞ ጀምሯል።

የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡ የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ደግሞ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ከሁለቱም ወገኖች ጋር ማክሰኞ አስቸኳይ ውይይት መጥራታቸው ተነግሯል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለው የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሥራ ማቆም አድማ ለመንገደኞች እንግልት መፍጠሩ ተገለፀ
በናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለው የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሥራ ማቆም አድማ ለመንገደኞች እንግልት መፍጠሩ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.02.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0